ለወገን ደራሸ ወገን ነው – ሪፍት ቫሊ የዩኒቨርስቲ ለተፈናለው ማሀበረሰብ ዕርዳታ ዓደረገ

የሪፍት ቫሊ የዩኒቨርስቲ በጌዲዖ  ዞንና በአማራ ክልል ተፈናቅለው በመጠሊያ ሥር ለሚገኙ  ወገኖቻችን ዕርዳታ ሰጠ

0
1461

የሪፍት ቫሊ የዩኒቨርስቲ በጌዲዖ  ዞንና በአማራ ክልል ተፈናቅለው በመጠሊያ ሥር ለሚገኙ  ወገኖቻችን ዕርዳታ ሰጠ።


የሪፍት ቫሊ የዩኒቨርስቲ የአመራር አካላት ከዚህ በፈት በሀገርቷ በተፈጠረው  ለውጥ ጋር  ተያይዞ  በተፈጠረው የፀጥታ አለመረጋጋት የተነሳ ለተፈናቀሉ ወገኖቻችን የበኩሉን ድጋፍና ዕገዛ ሲያደርግ ቆይቷል። በአሁኑ ወቅትም ዩኒቨርስቲው ተመሳሳይ ሁኔታ  በገዲዖ ዞን በገደብ መጠለያ ጣቢያ ተጠልለው ለሚገኙ  ተፌናቃዮች ወደ አንድ ነጥብ አራት ሚልዩን ብር የሚገመት ሞኮሮንና ዱቄት በዕርዳታ መልክ  አበረከተ ።

 

አቶ ፍቃዱ ደያሳ የሪፍት ቫሊ ዩኒቨርስቲ ም/ኘሬዝዳንት ተፈናቃዩቹ ላይ በደረሰው እንግልት ማዘናቸውን ገልፀው ለወደፊት ተፈናቃዪቹን መልሶ ለማቋቋም በሚደረገው ጥረት ውሰጥ አቅም በፈቀደ መጠን ተመሳሳይ ዕገዛና ድጋፍ እንደሚደረግላቸው ቃል ገብተዋል ።

 

 

ዩኒቨርስቲው በተመሳሳይ ሁኔታ  በአማራ ክልል ለተፈናቀሉ ወገኖቻችን አንድ ሚሊዮን ብር በዕዳታ  አበርክቷል።

2.ሪፋት ቫሊ ዩኒቨርስቲ ወደ ስድሰት መቶ ሺ ብር የሚገመት የመማሪያ ቁሳቁሶችን ለሁለተኛ ከፍተኛ ደረጃ ት/ቤቶች አበረከተ።

የዩኒቨርስቲው ባለቤት አቶ ዲንቁ ዴያሳ ድጋፍ ለሌላቸውን ችግርተኛ ተማሪዎች ነፆና ግማሽ ክፍያ በመክፍል መማር እንድችሉ በማድረግ ብዙዎች የሥራ ባለቤት ማድረጋቸው ይታወቃል ፣አሁንም በማድረግም ላይ ይገኛሉ ።የዚሁ ጥረት አካል የሆነው ድጋፍና ዕገዛ በአምቦ ለአዋሮ ፣በአአ ዙሪያ ለሜታ ጉታ ኮምቦሌ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ተበርክቶላቸዋል። የተሰጡ ቁሳቁሶች የተለያዩ መጽሐፍት፣ ኮምፒዩተሮችና ጠረጴዛዎችን  ያጠቃልላል ።ይህ ድጋፍ አቅም በፈቀደ መጠን በሌሎችም ከፍተኛ ችግር ላለባቸው ት/ቤቶችን ለወደፊትም እንደሚደረግ አመራሩ  ቃል ገብተዋል ።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here