የሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር እና የልማት ክንፍ በየቅርንጫፎቹ ተመድበው በማገልገል ላይ ለሚገኙ አካውንታቶች ‘አለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርትንግ እሰታንዳርድ’ በሚል ርዕሰ ከሰኔ 3ቀን 2011ዓም ጀምሮ ለአምሰት ተከታታይ ቀናት ሰልጠና ተሰጥቷል ።
ስልጠናው በአቶ አለማየሁ ኩማ የዩኒቨርስቲው የፋይናንስ ዳይሬክተር የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር የተከፈተ ሲሆን አቶ አለማየሁ በንግግራቸው ስልጠናው የአካውንታቶቹን አቅም በማሳደግ የሚጠበቅባቸውን ሥራ በአግባቡ እንድወጡ ለማስቻል ታሰቦ የተከናወነ መሆኑን አስረድተው አቶ ፍቃዱ አሸናፊ የሪፍት ቫሊ የአስተዳደር እና የልማት ም/ኘሬዝዳንት የመክፈቻ ንግግር እንድያደርጉ በመጋበዝ ንግግራቸው አጠናቀዋል ።
አቶ ፍቃዱ በበኩላቸው ሰልጠናው አለም አቀፍ ደረጃን የጠበቀ ወቅታዊ ሰልጠና በመሆኑ ሰልጣኞቹ ስልጠናውን ንቃት በተሞላበት ሁኔታ ተከታትለው ወደመጡበት ካምፓሰ ሲመለሱ ይኸንን እውቀትና ክህሎት በተግባር ላይ በማዋል ለተማሪዎች ፣ለባለድርሻ አካላት ቀልጣፋ እና ውጤታማ አግልግሎት መሰጠት እንዳለባቸው አሳሰበው ተመሳሳይ ሰልጠና እንደአሰፈላጊነቱ አየታየ አንደሚሰጥ ቃል ገብተው ንግግራቸው ቋጭተዋል።
ሰልጣኞች በስልጠናው ወቅት በንድፈ ሀሳብ ደረጃ የተማሩትን በተግባር እንድለማመዱ እና ጥያቄዎችን እንድጠይቁ አሰፈላጊው ዕገዛ በተመደቡ ባለሙያዎች ተደርጎላቸዋል ።
ስልጠናው በታለመለት ዕቅድ መሠረት ባለፈዉ አርብ ተጠናቋል ።በማጠቃለያ ላይ ሰልጣኞች የቀሰሙትን ዕውቅና ክህሎት በተግባር በማዋል የካምሱን ሠራተኞች፣ ተማሪዎች እና ባለድርሻ አካላት ተጠቃሚ እንድያደርጉ ማሳሰቢያ ከተሰጠ በኋላ የተሳትፎ የምስክር ወረቀት ተሰጥተዋል ።
ከዚህ በታይ የሚታዩ ፎቶግራፎች ሰልጣኞቹ በሰልጠና ላይ እያሉ የተወሰዱ ናቸው።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here