የሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ መልዕክት

ለ2012 ዓ.ም ዕጩ የጤና ምሩቃን እና የዪኒቨርሲቲዉ ማህበረሰብ

አስቸኳይ ሙያዊ የእርዳታ ጥሪ

በአሁኑ ጊዜ ሀገራችንን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት በኮሮና ቫይረስ  ወረርሽኝ እየተናወጡ ይገኛሉ። በሽታው እየተባባሰ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ ሀገራት በርካታ እርምጃዎችን እየወሰዱ መሆናቸውን ከተለያዩ የመገናኛ አዉታሮች እየሰማን ነው ። የኢትዮጵያ መንግሥትም የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት በርካታ ሥራዎችን እየሰራ ነው ። የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በመንግሥት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ልወስዱ በሚገባቸው ጥንቃቄዎች ዙርያ ሰፊ ስራ በመስራት ላይ ይገኛል። የከፍተኛ ትምህርት አግባብነት እና ጥራት ኤጀንሲም የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በሽታውን ከመከላከል አኳያ የራሳቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ጥሪ አድርጓል ።
ስለዚህ ሪፍት ቫሊ ዪኒቨርሲቲ እንደ ሀገር የተጋረጠብንን ፈተና ከህዝባችን ጎን ሆነዉ የበኩላቸዉን ሙያዊ እና ሰብዓዊ ሀላፊነት እንዲወጡ ሲል ለዘንድሮ የጤና ተመራቂዎቹ እና ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ጥሪ ያደርጋል።
የዕዉቀታችሁ ፍሬ ለሰው ልጅ መዋል       ካለበት ወቅቱ አሁን መሆኑን ተገንዝባችሁ አሁኑኑ በዚህ የስልክ ቁጥር ………ላይ ደዉላችሁ እንድትመዘገቡ ትጠይቃላችሁ ።ለአገልግሎት የሚጠቅሙ ሥልጠናዎችን ከጤና  ሚኒስቴር  ጋር የሚያመቻች መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ከወዲሁ ያሳዉቃል።
ሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here